ሐጅን አስመልክቶ አንዳንድ መረጃዎች
=============

© @The Ethiopian Islamic Affairs Supreme Council

የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ምክር ቤት መጪውን ሐጅ አስመልክቶ ቅድመ ዝግጅት እያደረገ ሲሆን የተበላሹ አሠራሮችን ለማስተካከልም ጥረት በማድረግ ላይ ይገኛል። ለጊዜው በሐጅ ዙሪያ የሚከተሉትን መረጃዎች ልናቀርብ እንወዳለን:‐

⑴ የዚህ ዓመት ሐጅ የክፍያ መጠን ብር 78,150.00 ተደርጓል፤

⑵ የሐጅ ምዝገባ የሚጀመረው ሰኔ 1/2011 ይሆናል፤

⑶ የምዝገባው ሂደት ሙሉ ለሙሉ የሚካሄደው በተማከለ አሠራር በፌደራል እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት ብቻ ይሆናል፤

⑷ ባለው የጊዜ እጥረት ምክንያት በክልል የእስልምና ጉዳይ ምክር ቤቶች በኩል የሚሠራ የማጣሪያ ሂደት አይኖርም፤

ምክር ቤታችን ከላይ ከተቀመጡት ውሳኔዎች አንጻር ሐጃጆች ቅድመ ዝግጅት እንዲያደርጉ እያሳሰበ የተሳካ እና ተቀባይነት ያለው መንፈሳዊ ጉዞ ይሆን ዘንድ ከወዲሁ ምኞቱን ይገልጻል!

Leave a comment