ስለየወደፊቱ መጅሊስ ህጋዊ ማዕቀፍና መዋቅራዊ ሁኔታ በተቋማዊ ለውጥ የጋራ ኮሚቴ የተሠሩ ጥናቶች ለዉይይት እየቀረቡ ነው።

።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ም/ቤት(መጅሊስ) በጠንካራ መሠረት ላይ ለማቆም በኢትዮጵያ ሙስሊሞች ተቋማዊ ለውጥ የጋራ ኮሚቴ በተቋቋሙ ሦስት ንዑስ ኮሚቴዎች አማካኝነት እየየተሰሩ የነበሩት ጥናቶች ረቂቅ ጥናቶች ለዉይይት እየቀረቡ ነው።

1) የተቋሙን የህጋዊ ማዕቀፍና ህጋዊ ሰውነት ላይ በህግ ባለሞያዎች የተሠሩት አማራጭ ረቂቆች ላይ የባለፈው እሁድ ለህግ ባለሞያዎችና ዉስን ባለድርሻ አካላት ቀርቦ አስተያየት የተሠጠበት ሲሆን ዛሬ ጠዋት ደግሞ ቀጣዩ ክፍል ላይ ሙስሊም ጠበቆች፣ዳኞችና አቃቢ ህጎች ብቻ ተገኝተው ከህግ አንፃር አስተያየት በመስጠት ሰነዶቹን ያዳብራሉ።

2) የመጅሊስ የዉስጣዊ አደረጃጀትና የምርጫ ሁኔታ ላይ በአህመዲን ጀበል የሚመራው 14 አባላት ያሉት የባለሞያዎች ንዑስ ኮሚቴ የተሠራው ረቂቅ ሰነድ ነገ ጥሪ የተደረገላቸው 100 የሚሆኑ ባለድርሻ አካላት በተገኙበት ነገ እሁድ ሙሉ ቀን ዉይይት ይደረጋል። በዚህ የመጀመሪያ ዙር በአዲስ አበባ የሚገኙ የቀድሞ የመጅሊስ አባለት፣የአሁኑ መጅሊስ አባላትና መጅሊስን ለማሻሸል በተለያዩ ጊዜያት የተለያዩ አማራጭ ሰነዶችን ያዘጋጁ ግለሰቦችና ተቆርቋሪ ግለሰቦች በመድረኩ ተገኝተው አስተያየት ይሰጡበታል። በመጀመሪያው ዙር ዉይይት ላይ በሚገኙ ግብአቶች ከዳበረ በሗላ ከመላ ሀገሪቱ የተጠሩ ባለድርሻ አካላት አስተያየት እንዲሰጡበት ይደረጋል። ለሰፊው ህዝብም ይሰራጫል።

3) ከዚህ በፊት በአዲስ አበባ ለሚገኙ ዑለሞች ቀርቦ አስተያየት የተሰጠበት የአንድነትና የትብብር ሰነድ ከመላ ሀገሪቱ በቅርቡ ዑለሞች ጥሪ ተደርጎላቸው ሰበዱ ቀርቦ ዉይይት ከመደረጉ ከዚህ በፊት በተሰጡ ግብኣቶች የዳበረው ረቂቅ የፊታችን ሰኞ 40 ለሚሆኑ ዑለሞች በድጋሚ ይቀርባል።

እነዚህ ሦስቱ ሰነዶች ሲፀድቁ በአዲሱ አወቃቀር መሠረት በቅርቡ በመላ ሀገሪቱ የመጅሊስ ምርጫ ይደረጋል ተብሎ ይጠበቃል።

Leave a comment