ለተከበራችሁ የደሴ እና አካባቢዋ ሙስሊሞች እንዲሁም መላው የአማራ ክልል ህዝብ፣
*******************************************
🚧 ነገ በደሴ ሊካሄድ የታቀደው ህዝባዊ መድረክ ተሰርዟል!!
*******************************************
የጠቅላይ ሚኒስትር ጽ/ቤት እና የኢትዮጵያ ዋና ዋና የቴሌቪዥን ጣቢያዎች እንዳሳወቁት ዛሬ በባሕርዳር በክልሉ መንግስት ላይ የመፈንቅለ መንግስት ሙከራ መደረጉ ታውቋል። የመፈንቅለ መንግስት ሙከራውን በግሌ እና በመላው ሙስሊም ማህበረሰብ ስም አጥብቄ አወግዛለሁ።

ከሙከራው ጋር ተያይዞ የደረሰ ጉዳት እና አጠቃላይ የክልሉን የፀጥታ ሁኔታ አስመልክቶ ዝርዝር መግለጫ እንደሚሰጥ ብንጠብቅም በአሁኑ ሰአት የፌዴራል መንግስት የፀጥታ ሀይል ሁኔታዎችን የመቆጣጠርና የማረጋጋት ስራ እንዲሰራ መታዘዙ ተነግሯል። በመሆኑም የህዝቡን እና የአካባቢውን ሁኔታ ከስጋት ለመታደግ እንዲሁም ጉዳዩን በጥንቃቄ መያዝ ስለሚያስፈልግ በተጨማሪም የፌዴራል እና የክልሉ መንግስት ለሚያደርጉት የማረጋጋት ስራ ምቹ ሁኔታ ለመፍጠር ሲባል በነገው እለት በደሴ ስታዲየም ታስቦ የነበረው ህዝባዊ መድረክ መሰረዙን አስተባባሪዎቹ ጋር በተደረገ ውይይት ተወስኗል። ለደሴና አካባቢው ማህበረሰብ እንዲሁም ለመላው የአማራ ክልል ህዝብ ሁኔታዎችን በተረጋጋ እና ኃላፊነት በተሞላበት መልኩ እንድትይዙት አደራ እያልኩኝ አላህ ለህዝባችን እና ለሀገራችን ዘላቂ መረጋጋት እንዱያመጣ እለምናለሁ። ህዝቡም የበኩሉን ድርሻ እንዲወጣ አደራ እላለሁ።

Leave a comment