ጠቅላይ ሚስትር ዶ/ር አብይ አህመድ በተገኙበት ከተስፋ አዲስ የወላጆችና የህፃናት የካንሰር ድርጅት ታካሚዎች ጋር የኢድ አልፈጥር በዓለን እያከበርን እንገኛለን

ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር ዐቢይ አሕመድን ጨምሮ ከተስፋ አዲስ የወላጆችና የህፃናት የካንሰር ድርጅት ታካሚዎች ጋር የኢድ አልፈጥር በዓለን በማክበር ላይ እንገኛለን::

ከጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር አብይ አህመድ ጋርም የኢፌዴሪ የጤና ሚኒስትር ዶክተር አሚር አማን፣ የአዲስ አበባ ምከትል ከንቲባ ኢንጂነር ታከለ ኡማ፣አስታዝ አቡበከር አህመድ፣ኡስታዝ መሐመድ አባተ እና ሌሎችም በተገኙበት ከታማሚዎቹ ጋር በመሆን ኢድን በማክበር ላይ እንገኛለን::

ኢድን ስናከብር ከታማሚዎች፣ከአቅመ ደካሞች፣ከድሆች እና ከተፈናቀሉ ወገኖቻችን ጋር ሊሆን ይገባል::

የዛሬውን ኢድ እያከበርንበት የሚገኘው ድርጅቱ የካንሰር ህመምተኛ ለሆኑ ህፃናት እና ወላጆቻቸው የማማከር አገልግሎት በመስጠት ላይ ይገኛል።

ይህ ማእከል በአንድ ጊዜ 50 ህጻናትን ከእነወላጆቻቸው ማስተናገድ የሚችል ነው።

ከኢድ ክብረ በዓሉ ጎን ለጎንም ችግኝ ተከላ ተካሂዷል::

በድጋሚ ለሁላችንም ኢድ ሙባረክ!

Leave a comment