ጠቅላይ ሚኒስተር ዶ/ር አብይ አህመድ በአዲስ አበባ ላሉ ሙስሊም አምባሳደሮች፣ ለሙስሊም ባለስልጣናት፣ ለሀገር ዓቀፍ ዑለማ ምክር ቤትና ቦርድ፣ ለኢትዮጵያ ሙስሊሞች ተቋማዊ ለውጥ የጋራ ኮሚቴና ለመፍትሄ አፈላ ላጊ ኮሚቴ አባላት፣ በቅርቡ ከስልጣን ለወረዱት የመጅሊስ አመራሮችና ጥሪ የተደረገላቸው ሌሎች ሙስሊሞች ትናንት ምሽት በስካይ ላይን ሆቴል ኢፍጣር ዝግጅት አድርገዋል። በዝግጅቱ ላይ ባደረጉት ንግግር:

1) “በኛ በኩል ከዚህ ቀደም አንኳር አንኳር የሆኑ የሙስሊሙን ጥያቄዎች በፍጥነት ለመመለስ ከምንጊዜውም በላይ ከጎናችሁ እንደምንቆም ላረጋጋጥላችሁ እፈልጋለሁ።”

2) “የጀመራችሁትን የይቅርታና የአንድነት ሂደት ሳይሰናከል ለዘላቂ ዉጤትና ስኬት እንደሚበቃ ሙሉ እምነት አለኝ።”

3) “አደራ አደራ የህዝበ ሙስሊሙ አንድነት የናንተ አጀንዳ ይሁን።”

4) ” የፊታችን እሁድ ሳምንት(የዛሬ ሳምንት) በሚደረገው ሀገር አቀፍ የፅዳት ዘመቻ አንድም ሙስሊም እንዳይቀር በአላህ ስም እጠይቃለሁ። የዑለማ ምክር ቤት ለህዝበ ሙስሊሙ ጥሪ እንዲያደርጉ እጠይቃለሁ። ኢድ አንድ ቀን ሲቀረው ደግሞ ኢትዮጵያውያን ክርስቲያኖች ለሙስሊም ወንድሞቻቸው የኢድ መስገጃ ቦታ በማፅዳት እንዲያዘጋጁ ጥሪ እናደርጋለን።”
5) “ሙፍቲ ለኢትዮጵያውያውን ሙስሊሞች ክብር ናቸው። ሁላችሁንም እወዳለሁ። ሙፍቲን ግን አስበልጬ እወዳለሁ።”

Leave a comment