የሐጅ ምዝገባን አስመልክቶ አስፈላጊ መረጃዎች
==============


© The ethiopian islamic affairs supreme council

የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት የ2011 የሐጅ ተጓዦችን ምዝገባ ለመጀመር ቅድመ ዝግጅቱን አጠናቋል። በመሆኑም ከሰኔ 1 ጀምሮ ለሚከናወነው ምዝገባ ተጓዦች የሚከተሉትን ቅድመ ሁኔታዎች በማሟላት ከ18 ማዞሪያ ወረድ ብሎ ሆላንድ ኤምባሲ አጠገብ በሚገኘው ዋና መሥሪያ ቤታችን በመገኘት ምዝገባ መጀመር እንደሚችሉ እናስታውቃለን።

ለምዝገባው የሚያስፈልጉ ቅድመ ሁኔታዎች፦

👉 የሐጅ ክፍያውን ብር 78,150.00 ከታች በተመለከቱት የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ፣ ኦሮሚያ ኢንተርናሽናል ባንክ ወይም ኦሮሚያ የኅብረት ሥራ ባንክ አካውንቶች ገቢ ያደረጉበትን ደረሰኝ፤

👉 ጊዜው ያላለፈበት ፓስፖርት፤

👉 ባለትዳሮች በጋራ የሚጓዙ ከሆነ የጋብቻ የምስክር ወረቀት፤

በቀረው ጥቂት ጊዜ ተመዝጋቢዎችን ከአላስፈላጊ እንግልት ለመታደግና በቅልጥፍና ለማሥተናገድ ይቻል ዘንድ ከክልሎችም ሆነ ከከተማ መሥተዳድሮች ለሚመጡ የሐጅ ተጓዦች ከየትኛውም የመጅሊስ ጽሕፈት ቤት የማጣሪያም ሆነ ሌላ ማንኛውም ዓይነት ምዝገባ እና ክፍያ የሌለ መሆኑን አጥብቀን እናሳስባለን። ከምዝገባው ጀምሮ ያሉት ሂደቶችም ካለፉት ጊዜያት የተሻለ ይሆን ዘንድ በተማከለ አሠራር በፌዴራል መጅሊስ ብቻ የሚሰጡ ይሆናል።

=====
የክፍያ መፈጸሚያ የባንክ ሂሳቦች
=====

👉 የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ
የሂሳብ ቁጥር፡ 1000028707127


👉 ኦሮሚያ ኢንተርናሽናል ባንክ
ኦዳ ቅርንጫፍ
የሂሳብ ቁጥር፡ 1083934/2010101/1


👉 የኦሮሚያ ኅብረት ሥራ ባንክ
የሂሳብ ቁጥር፡ 1000023158462


የኢትዮጵያ እስልምና ጉዳዮች ጠቅላይ ምክር ቤት

Leave a comment