የሰላም ሚኒስቴር የኢትዮጵያ ሙስሊሞች ተቋማዊ ለውጥ የጋራ ኮሚቴ አባላት የህዝበ ሙስሊሙን የተቋም ችግሮች ለመፍታት እንዲያስችል ለህዝበ ሙስሊሙ አንድነትና የመጅሊስ አመራር ለውጥ ስኬት ላይ ህዝቡን በመስተባበር ላሳዩት የላቀ አስተዋፅኦ አመስግኗል። የሰላም ሚኒስትሯ ወ/ሮ ሙፈሪያት ካሚል ለኮሚቴው አባላት ዛሬ በሸራተን አዲስ ሆቴል የምሳ ግብዣ በማድረግ የምስክር ወረቀት ሰጥተዋል።

Leave a comment