ጠቅላይ ሚኒስትር ዶክተር እብይ አህመድ ከኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን የሰንበት ተማሪዎች ጋር በመሆን ከፊታችን ለሚከበረዉ የኢድ በዓል ስታዲየም አካባቢን አፀዱ።

የሙስሊም ወንድምና እህቶች የአንድ ወር ረመዳን ፆም ማብቂያ በተመለከተ የክርስትና እምነት ተከታዮች አጋርነታቸዉን በጽዳት አሳይተዋል።

ካለፈው አርብ ጀምሮ በመላው ሀገሪቱ በጎ ፈቃደኛ ወጣቶች በጋራ በመሆን የአምልኮ ስፍራዎችን እና የኢድ ሶላት መስገጃ ስፍራዎችን ሲያፀዱ ቆይተዋል።

Photo Credit: Office of the Prime Minister-Ethiopia

Leave a comment