ማስታወሻ(1)

በሁሉም የሀገራችን አካባቢ ያለን ኢትዮጵያውያን ከምን ግዜውም በላይ ለህዝብ ደህንነት እና ለሰላም ቅድሚያ በመስጠት ላይ አደራ!

በየትኛውም የሀገራችን ክፍል ያለ ስጋት የመላው ህዝብ እና የአጠቃላይ የሀገር ስጋት ነው። በአንድ አካባቢ የተፈጠረ ስጋትም በሌሎች አካባቢዎች እንዳይዛመት የህዝቡ ሚና ከፍተኛውን ድርሻ ይይዛል። በመሆኑም መላው ኢትዮጵያውያን በተረጋጋ እና የሀገርን ሰላም ለማስከበር ለሚሰሩ የመንግስት አካላት ቀና ትብብር በማድረግ ላይ የበኩላችሁን እንድትወጡ በድጋሜ አደራ እላለሁ። በተለይም በመሬት ላይ ለሚያጋጥሙ ችገሮች መፍትሄያቸው ተግባራዊ ስራዎች በመሆኑ የማህበራዊ ሚዲያ አጠቃቀማችን በተግባር የሚካሄዱ የህዝባችንን ደህንነት የማስጠበቅ ስራ እንዳይጎዱ ከፍተኛ ጥንቃቄ እንድናደርግ አጥብቄ እጠይቃለሁ።

Leave a comment