All Posts

የህዝበ ሙስሊሙን አንኳር አንኳር ጥያቄዎችን በአፋጣኝ እንመልሳለን።”( ጠቅላይ ሚኒስተር ዶ/ር አብይ አህመድ)

ጠቅላይ ሚኒስተር ዶ/ር አብይ አህመድ በአዲስ አበባ ላሉ ሙስሊም አምባሳደሮች፣ ለሙስሊም ባለስልጣናት፣ ለሀገር ዓቀፍ ዑለማ ምክር ቤትና ቦርድ፣ ለኢትዮጵያ ሙስሊሞች ተቋማዊ ለውጥ የጋራ ኮሚቴና ለመፍትሄ አፈላ ላጊ ኮሚቴ አባላት፣ በቅርቡ ከስልጣን ለወረዱት የመጅሊስ አመራሮችና ጥሪ የተደረገላቸው ሌሎች ሙስሊሞች ትናንት ምሽት በስካይ ላይን ሆቴል ኢፍጣር ዝግጅት አድርገዋል። በዝግጅቱ ላይ ባደረጉት ንግግር:…

Read more

የሰላም ሚኒስተር የኢትዮጵያ ሙስሊሞች ተቋማዊ ለውጥ የጋራ ኮሚቴን የምስጋና ምስክር ወረቀት አበረከተ

የሰላም ሚኒስቴር የኢትዮጵያ ሙስሊሞች ተቋማዊ ለውጥ የጋራ ኮሚቴ አባላት የህዝበ ሙስሊሙን የተቋም ችግሮች ለመፍታት እንዲያስችል ለህዝበ ሙስሊሙ አንድነትና የመጅሊስ አመራር ለውጥ ስኬት ላይ ህዝቡን በመስተባበር ላሳዩት የላቀ አስተዋፅኦ አመስግኗል። የሰላም ሚኒስትሯ ወ/ሮ ሙፈሪያት ካሚል ለኮሚቴው አባላት ዛሬ በሸራተን አዲስ ሆቴል የምሳ ግብዣ በማድረግ የምስክር ወረቀት ሰጥተዋል።

Read more

የኡስታዝ አቡበከር አህመድ የምስጋና እና የደስታ መግለጫ!

የኡስታዝ አቡበከር አህመድ የምስጋና እና የደስታ መግለጫ! አልሃምዱሊላህ፣ አልሃምዱሊላህ፣ አልሃምዱሊላህ! ያለልዩነት ሲነሳ የኖረ የተቋም ጥያቄ ያለልዩነት ወደመፍትሄ በማምራቱ እንኳን ደስ አለን፣ እንኳን ደስ አላችሁ! ኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች ያለአንዳች ልዩነት ከግማሽ ክፍለ ዘመን በላይ በጋራ ሲያነሱት የቆዩትና መሰዋእትነት የከፈሉለት የነፃና እና ገለልተኛ ተቋም ጥያቄ ዛሬ በተካሄደው የተቋማዊ ለውጥ እና የአንድነት ጉባኤ አንድ…

Read more

ድላችን ደጃፍ ላይ ደርሷል

«ድላችን ደጃፍ ላይ ደርሷል!» «በዛሬው ስብሰባ የአገራችን እስልምና ታሪክ ወሳኝ ምእራፍ ላይ ደርሷል!» «አዲሱን የዑለማ ምክር ቤትና ቦርድ ማገዝ ኢስላማዊ ግዴታችን ነው!» የሚያዚያ 23/2011 ጉባኤን ስኬት አስመልክቶ ከ17ቱ የመፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ የተሰጠ መግለጫ ረቡዕ ሚያዝያ 23/2011 አዲስ አበባ/ኢትዮጵያ ©ድምፃችን ይሰማ ኢትዮጵያውያን ሙስሊሞች ዛሬ ሚያዚያ 23/2011 በተደረገው ስብሰባ የደረስንበት ደረጃ በታሪካችን…

Read more

ለዛሬዋ ቀን ላበቃን ጌታ ምስጋና ይገባው አልሀምዱሊላህ

ይህ ታሪካዊ ቀን እንዲመጣ ብዙ ዋጋ ተከፍሎበታል።የረጅም አመታት የህዝበ ሙስሊሙ የጠንካራ እና የነፃ ተቋም ባለቤትነት ጥያቄ ምላሽ እዉን ለመሆን ዛሬ መሰረቱን ተክሏል። ዉጤቱ የመላዉ ሙስሊም ማህበረሰብ ነዉና ለሁላችንም እንኳን ደስ አለን ለማለት እወዳለሁ ከፊታችን የመጣው የተከበረው የረመዳን ፆምንም በልዮ የደስታ የአንድነት : የይቅርታና በብሩህ መንፈስ የላቀ ዉጤት ለማስመዝገብ ወደ አሏህ…

Read more

የሚያዚያ 23ቱ ጉባኤ መሳካት የኢትዮጵያ ሙስሊሞች ጥያቄ መሳካት ጅምር ነው

#EthioMuslims #EthioMuslimCommittee **** «የሚያዚያ 23ቱ ጉባኤ መሳካት የኢትዮጵያ ሙስሊሞች ጥያቄ መሳካት ጅምር ነው!» «ይህን ጅምር ህዝቡ በንቃትና በጥንቃቄ እንዲከታተለው ጥሪያችንን እናስተላልፋለን!» «ኮሚቴያችን የህዝበ ሙስሊሙ ተቋም ህዝቡ በምርጫ በመረጣቸው መሪዎች በቋሚነት እስኪቋቋም ድረስ የህዝብ ውክልናውን ከግብ ለማድረስ ጥረቱን ይቀጥላል!» «በነገው ጉባኤ የሽግግር መጅሊስ ቦርድ በማቋቋም የመጅሊስ አመራሮችን መተካት ለድርድር የማይቀርብ የጉባኤው…

Read more

ኡስታዝ አቡበከር አሕመድ በሰሜን አሜሪካ በዩናይትድ ስቴትስና ካናዳ የነበራቸውን የሥራ ጉብኝት አጠናቅቀው ትናንት ማለዳ አዲስ አበባ ገብተዋል፡፡

ኡስታዝ አቡበከር አሕመድ በሰሜን አሜሪካ በዩናይትድ ስቴትስና ካናዳ የነበራቸውን የሥራ ጉብኝት አጠናቅቀው ትናንት ማለዳ አዲስ አበባ ገብተዋል፡፡ በጉብኝታቸው በዩናይትድ ስቴትስ ቴክሳስና ሲያትል ግዛቶች እንዲሁም በሀገረ ካናዳ በቶሮንቶ፣ ዊንፔግ፣ ካልጋሪና ኤድመንተን ከሚገኙ የሙስሊም ኢትዮጵያውያን ማኅበረሰብ አካላት ጋር ተገናኝተዋል፡፡ በከተሞቹ በተዘጋጁ የመድረክ ፕሮግራሞችም በርካታ ኢትዮጵያውያን የተሳተፉ ሲኾን፣ ኡስታዝ አቡበከርም የዳያስፖራው ማኅበረሰብ አባላት…

Read more

የሚያዝያ 23ቱ ጉባኤ የሚደናቀፍ ከሆነ አገር አቀፍ ሰልፍ እንጠራለን!

«የሚያዝያ 23ቱ ጉባኤ የሚደናቀፍ ከሆነ አገር አቀፍ ሰልፍ እንጠራለን!» የሚያዝያ 23ቱን ጉባኤ አስመልክቶ ከ17ቱ የሙስሊም መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ የተሰጠ መግለጫ ቅዳሜ ሚያዝያ 19/2011 አዲስ አበባ/ኢትዮጵያ **** ©ድምፃችን ይሰማ የፊታችን ረቡዕ 300 ዑለሞች እና ምሁራን በሚሳተፉበት ጉባኤ የዑለማ ምክር ቤት እና የመጅሊስ ባለአደራ አሥተዳደር እንደሚቋቋም በተቋማዊ ለውጥ ኮሚቴው መገለጹ ይታወሳል። ይህ…

Read more

መጅሊሱ ሁሉንም ሙስሊም የሚሰበስብ መጠለያ ተቋም ሊሆን ይገባል

«መጅሊሱ ሁሉንም ሙስሊም የሚሰበስብ መጠለያ ተቋም ሊሆን ይገባል!» «መጅሊሱን የአንድ ቡድን የተለየ መጠቀሚያ የሚያደርጉ አካሄዶች እንዲኖሩ አንፈቅድም!» የተቋማዊ ለውጥ ኮሚቴው የሰጠውን መግለጫ አስመልክቶ ከ17ቱ የሙስሊም መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ የተሰጠ መግለጫ ዓርብ ሚያዝያ 18/2011 አዲስ አበባ/ኢትዮጵያ **** ©ድምፃችን ይሰማ በትናንትናው ዕለት የተቋማዊ ለውጥ ኮሚቴው የደረሰበትን የሥራ ደረጃ በመግለጫ አማካኝነት ይፋ አድርጓል።…

Read more